Genesis Systems · Legal Notice
⚠️

ይፋዊ ማስታወቂያ፡ የድረ-ገጽ እና የሲስተም አገልግሎት መቋረጥ

ለዩኒየን አካዳሚ (Union Academy Hawassa) ተማሪዎች፣ ወላጆች እና ማህበረሰብ በሙሉ የተላለፈ

📌 ማብራሪያ እና የስራው አፈጻጸም ሁኔታ

ይህ ድረ-ገጽ እና ተያያዥ የፈተና መለማመጃ የሞባይል መተግበሪያ (LMS) በጄኔሲስ ሲስተምስ (Genesis Systems) እና በትምህርት ቤቱ አስተዳደር መካከል በተደረገው ህጋዊ የውል ስምምነት መሰረት ሙሉ በሙሉ ተገንብቶ፣ ተፈትሾ እና ወደ ስራ ገብቶ የነበረ መሆኑ ይታወቃል።

ሲስተሙ ከ250 በላይ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በኮምፒውተር ላብራቶሪ ውስጥ በአንድ ጊዜ ሞዴል ፈተና የወሰዱበትን የስርዓት መቋቋም ሙከራ (Stress Test) ጨምሮ ለተከታታይ ሳምንታት ያለምንም እንከን መስራቱ በትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ እዮብ ፅጌ ፊት በአካል ተመስክሯል።

⚖️ አገልግሎቱ ለምን ተቋረጠ? (የውል ጥሰት)
በርዕሰ መምህሩ በተፈረመው ህጋዊ ውል መሠረት ስራው ተጠናቆ ርክክብ ሲደረግ መከፈል የነበረበት ቀሪ 50% ክፍያ (15,000 የኢትዮጵያ ብር) እስካሁን ድረስ አልተከፈለም። የትምህርት ቤቱ አስተዳደር ተደጋጋሚ የክፍያ ቀጠሮዎችን ሳያከብር የቀረ ሲሆን፣ በውስጥ የፋይናንስ አሰራር ችግር ምክንያት የተጠየቁት ተጨማሪ ቀናት ቢያልቁም ክፍያው ሳይፈጸም ቀርቷል።

በመሆኑም በውል ስምምነቱ አንቀጽ 2.3 (የአእምሮአዊ ንብረት መብት) በተሰጠን ህጋዊ መብት መሰረት፣ ክፍያው እስኪፈጸም ድረስ ድረ-ገጹና የሲስተም አገልግሎቶቹ ሙሉ በሙሉ እንዲቋረጡ ተደርጓል።

🔄 አገልግሎቱ ዳግም እንዲጀምር ትምህርት ቤቱ ምን ማድረግ አለበት?
  • 1
    ቀሪ ክፍያን ማጠናቀቅ፦ ትምህርት ቤቱ በውሉ መሠረት ያለበትን ቀሪ 15,000 ብር (ጉዳዩ ወደ ህግ ከተላለፈ አንቀጽ 8.1 የሚደነግገውን የ10,000 ብር የውል ማፍረሻ ቅጣት ጨምሮ) ከዚህ በታች ባለው የባንክ ሂሳብ ገቢ ማድረግ።
  • 2
    ደረሰኝ ማቅረብ፦ የተከፈለበትን የባንክ ማረጋገጫ በኢሜይል አድራሻችን Paulteshale@hotmail.com መላክ።
  • 3
    ርክክብና ዳግም ማስጀመር፦ ክፍያው እንደተረጋገጠ የሲስተሙ ሙሉ የአስተዳዳሪ ቁጥጥር (Credentials) ለትምህርት ቤቱ ተላልፎ አገልግሎቱ ወዲያውኑ ወደ ስራ ይመለሳል።

የክፍያ አድራሻ (Official CBE Account)

የባንክ ስም
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE)
የሂሳብ ቁጥር
1000081235019
የሂሳብ ባለቤት
ጳውሎስ ተሻለ ይልማ